Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 49:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 “ኤዶምያስም መሣቀቂያ ትሆናለች፥ የሚያልፍባትም ሁሉ ይሣቀቃል፥ ስለ ተደረገባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ኤዶም የድንጋጤ ምልክት ትሆናለች፤ ከቍስሎቿም ሁሉ የተነሣ፣ በዚያም የሚያልፉ ሁሉ ወይ ጉድ! ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤዶም የምታስደነግጥ ትሆናለች፤ በዚያ በኩል ሲያልፍ የሚያያት ሁሉ ይደነግጣል፤ በደረሰባት ጥፋትም ይገረማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “ኤዶ​ም​ያ​ስም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባ​ትም ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ስለ መጣ​ባ​ትም መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ ያፍ​ዋ​ጭ​ባ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ኤዶምያስም መደነቂያ ትሆናለች፥ የሚያልፍባትም ሁሉ ይደነቃል፥ ስለ መጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 49:17
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል።


ምድራቸውን ለመሣቀቂያና ለዘለዓለም ማፍዋጫ አድርገዋል፤ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ይነቀንቃል።


ባሶራ መሣቀቅያና መሰደቢያ፥ ባድማና መረገሚያ እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ከተሞችዋም ሁሉ ለዘለዓለም ባድማ ይሆናሉ።”


ከጌታ ቁጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይሣቀቃል በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።


ባቢሎንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮ ማደሪያ ሰውም የማይቀመጥባት መሣቀቅያና ማፍዋጫ ትሆናለች።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።


ከሕዝቦች መካከል ያሉ ነጋዴዎች አፏጩብሽ፤ አስደንጋጭ ሆነሻል፥ ለዘለዓለምም አትገኚም።


የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በመሆኑ እንደተደሰትህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ፥ አንተ፥ ኤዶም ሁሉና ሁለንተናዋ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


እንዲህም በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሴይር ተራራ ሆይ፥ እነሆ በአንተ ላይ ነኝ፥ እጄን እዘረጋብሃለሁ ባድማና ውድማም አደርግሃለሁ።


የሴይርን ተራራ ውድማና ባድማ አደርገዋለሁ፥ የሚሄደውንና የሚመለሰውንም ከእርሱ አጠፋለሁ።


የዖምሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቀሃልና፥ በምክራቸውም ሄዳችኋልና፤ ስለዚህ አንተን ለጥፋት ነዋሪዎቿን ደግሞ ለመዘባበቻ ሰጥቻችኋለሁ፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።


“የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሪቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና ጌታ ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች