ኤርምያስ 49:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ከጌታ ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ “ተሰብሰቡ፥ በእርሷም ላይ ኑ ለጦርነትም ተነሡ” የሚል መልእክተኛ ተልኮአል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤ “እርሷን ለመውጋት ተሰብሰቡ፤ ለጦርነትም ውጡ” የሚል መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኳል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 አንድ መልእክት ከእግዚአብሔር ሰምቼአለሁ፤ “በኤዶም ሕዝብ ላይ አደጋ ለመጣል ተሰብሰቡ! ለጦርነትም ተነሡ!” ብሎ የሚናገር መልእክተኛ ወደ ሕዝቦች ተልኮአል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 “ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማትን ሰምቻለሁ፤ በአሕዛብ ሀገሮች ተሰብሰቡ፤ በእርስዋም ላይ ኑ፤ እርስዋንም ውጓት፥ የሚል መልእክተኛ ተልኳል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ ተሰብሰቡ፥ በእርስዋም ላይ ኑ ለሰልፍም ተነሡ የሚል መልእክተኛ ተልኮአል። ምዕራፉን ተመልከት |