Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 49:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የመሸሸጊያውንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ እርሱም ለመሸሸግ አይችልም፤ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እኔ ግን ዔሳውን አራቍተዋለሁ፤ መደበቅም እንዳይችል፣ መሸሸጊያ ስፍራዎቹን እገልጣለሁ፤ ልጆቹ፣ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ይጠፋሉ፤ እርሱም ራሱ አይኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔ ግን የዔሳውን ዘር በፍጹም አራቊታቸዋለሁ። የሚሸሸጉበትንም ስፍራ አጋልጣለሁ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ የሚሸሸጉበት ስፍራ ማግኘት አይችሉም፤ ልጆቻቸው፥ ዘመዶቻቸውና ጐረቤቶቻቸው ይጠፋሉ፤ እነርሱም አይኖሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እኔ ግን ዔሳ​ውን አራ​ቆ​ት​ሁት፤ የተ​ሸ​ሸ​ጉ​ት​ንም ስፍ​ራ​ዎች ገለ​ጥሁ፤ ይሸ​ሸ​ግም ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ዘሩም፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፤ ጎረ​ቤ​ቶ​ቹም ጠፍ​ተ​ዋል፥ እር​ሱም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የተሸሸጉትንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ ይሸሸግም ዘንድ አይችልም፥ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 49:10
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመሸ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሽብር አለ! ከመንጋቱም በፊት አንዳቸውም አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች እድል ፈንታ፥ የበዘበዙንም ዕጣ ይህ ነው።


“ያዕቆብን ወደድሁ፥ ኤሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።


ቴማን ሆይ፥ ሰዎች ሁሉ ከዔሳው ተራራ በግድያ እንዲጠፉ ኃያላን ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ።


በቀርሜሎስም ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳ አድኜ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ እንኳ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤


ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ይላል ጌታ። ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል ጌታ።


በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።


ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል።


ታው። የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የበደልሽ ቅጣት ተፈጸመ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም። የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ በደልሽን ይቀጣል፥ ኃጢአትሽን ይገልጣል።


ዔሳው ምንኛ ተበረበረ! ብርቅዬ ሀብቱ ምንኛ ተፈለገ!


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች