Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 48:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት ስለ ትምክህቱም ስለ ኩራቱም ስለ እብሪቱም ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ እብሪቱና ስለ ኵራቱ፣ ስለ ትምክሕቱና ስለ መጓደዱ፣ ስለ ልቡም ማበጥ ሰምተናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሞአብ በከፍተኛ ኲራት፥ ራሷን ከፍ ከፍ በማድረግ በትዕቢተኛነት፥ በመጀነንና በልበ ደንዳናነት የተወጠረች መሆንዋን ሰምቼአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 የሞ​አ​ብን ስድብ፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንም ብዙ ውር​ደ​ቱን፥ ልቡ​ና​ው​ንም ያስ​ታ​በ​የ​በ​ትን ትዕ​ቢ​ቱን ሰም​ተ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት ስለ ትምክህቱም ስለ ኵራቱም ስለ መጓደዱም ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 48:29
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ከፍ ያለ ነውና፥ ዝቅተኞችን ይመለከታልና፥ ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ያውቃል።


ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።


ኩሩና ተጓዳጅ ሰው ፌዘኛ ይባላል፥ እርሱም በትዕቢት ቁጣ ያደርጋል።


በትዕቢት ከፍ ከፍ ያሉ ዐይኖች ያሉት፥ ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ።


ጌታን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፥ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም ንግግር እጠላለሁ።


ዓለምን ስለ ክፋቷ፤ ክፉዎችንም ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችን እብሪት እሽራለሁ፤ የጨካኞችንም ጉራ አዋርዳለሁ።


የሞዓብን ኩራት፥ እጅግ መታበዩን! ስለ እብሪቱና ስለ ኩራቱ፥ ስለ ስድነቱም ሰምተናል፤ ትምክሕቱ ከንቱ ነው።


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”


ስለዚህ፥ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” እንደሚል፥ የሚሰጠው ጸጋ ግን ከሁሉም ይበልጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች