Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 46:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ውርደትሽን ሰምተዋል፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሕዝቦች ኀፍረትሽን ይሰማሉ፤ ልቅሶሽም ምድርን ይሞላል። ጦረኛ በጦረኛው ይደናቀፋል፤ ሁለቱም ተያይዘው ይወድቃሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሕዝቦች ሁሉ ስለ ኀፍረትሽ ሰምተዋል፤ የዓለምም ሕዝብ ሁሉ ጩኸትሽን አድምጠዋል፤ አንዱ ወታደር ሌላውን ወታደር ሲያደናቅፈው ሁሉም ተያይዞ መሬት ይወድቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ጦረ​ኞች በጦ​ረ​ኞች ላይ ተሰ​ና​ክ​ለው ሁለቱ በአ​ን​ድ​ነት ወድ​ቀ​ዋ​ልና አሕ​ዛብ ቃል​ሽን ሰም​ተ​ዋል፤ ልቅ​ሶ​ሽም ምድ​ርን ሞል​ቶ​አ​ታል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ጕስቍልናሽን ሰምተዋል፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 46:12
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈጣኑ መሸሽ አይችልም ኃያሉም አያመልጥም፤ በሰሜን በኩል ባለው በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ እነርሱ ተሰናክለው ወደቁ።


“ይሁዳ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ፤ ስለ ምድሪቱም አለቀሱ፤ የኢየሩሳሌም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሏል።


ግብፃውያንን በግብፃውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድም ወንድሙን፥ ባልንጀራም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።


በዚያ ቀን ይላል ጌታ፥ “የዓሣ በር” የጩኸት ድምፅ፥ ከከተማውም በሁለተኛው ክፍል ዋይታ፥ ከኮረብቶቹም ታላቅ ሽብር ይሆናል።


ከባቢሎን ጩኸት፥ ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰምቶአል።


ከመውደቃቸው ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፥ የጩኸትም ድምፅ በኤርትራ ባሕር ተሰማ።


ከሐሴቦን ጮኹ እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን አሰሙ፤ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ደርሶአል፤ የኔምሬም ውኃ ደግሞ ይደርቃል።


ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።


ያልሞቱትን ደግሞ ዕባጩ ያሠቃያቸው ስለ ነበር፥ የከተማዪቱ ጩኸት እስከ ሰማይ ወጣ።


ስለ ወይኑም ጠጅ በአደባባይ ጩኸት ይሆናል፤ ደስታ ሁሉ ጨልሞአል፥ የምድርም ሐሤት ፈርሶአል።


መንገድሽን ለመለወጥ ለምን በጣም ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ እንዲሁ ያሳፍርሻል።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ጐርፍ ይሆናል፤ በአገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።


ባቢሎን ስትያዝ ከነበረው የሁካታ ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፥ ጩኸትም በአሕዛብ መካከል ተሰማ።


ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይከንፋሉ፥ በአደባባዮችም ወዲህና ወዲያ ይጣደፋሉ፤ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች