Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 43:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ የጌታን ድምፅ አልሰሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና፣ የጦር መኰንኖቹ ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ በሙሉ እግዚአብሔር በይሁዳ ምድር እንዲቀመጡ ያዘዛቸውን ቃል አልሰሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በዚህም ዐይነት ዮሐናንም ሆነ የሠራዊት አለቆች ሁሉ፥ እንዲሁም ከሕዝቡ ወገን ማንም በይሁዳ ምድር ለመኖር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልፈጸሙም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ በይ​ሁዳ ምድር ይቀ​መጡ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይቀመጡ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 43:4
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህም የተነሣ ባቢሎናውያንን ስለ ፈሩ እስራኤላውያን ሀብታሞችም ድኾችም ከጦር ሠራዊት መኰንኖች ጋር በአንድነት ተነሥተው ወደ ግብጽ ሸሹ።


እርሱም እየተናረ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በውኑ አንተ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሾመነሃልን? ተው፤ እንዲገድሉህ ለምን ትሻለህ?” ነቢዩም፦ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና ጌታ ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ተወ።


በጌታ ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።


እኔም፦ ከኃይል ይልቅ ጥበብ ትበልጣለች፥ የድሀው ጥበብ ግን ተናቀች ቃሉም አልተሰማችም አልሁ።


የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ እርሱና ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ከምጽጳ ያስመለሱአቸውን የሕዝቡን ትሩፍ ሁሉ፥ እንዲሁም ከገባዖን ያስመለሱአቸውን ወታደሮች፥ ሴቶችንም፥ ልጆችንም፥ ጃንደረቦችንም፥ ወሰዱ፤


እኔም ዛሬ ነገርኋችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እናንተ በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የጌታን ድምፅ አልሰማችሁም።


ኤርምያስም የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆች ሁሉ፥ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡንም ሁሉ ጠራ፥


ነገር ግን አልሰሙም ከክፋታቸውም ተመልሰው ለሌሎች አማልክት ላለማጠን ጆሮአቸውን አላዘነበሉም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች