Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 42:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እናንተ የይሁዳ ትሩፍ ሆይ! እንግዲህ አሁን የጌታን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወደ ግብጽ ለመግባት በዚያም ሄዳችሁ ለመቀመጥ በእርግጥ ፊታችሁን ብታቀኑ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እንግዲህ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብጽ ለመሄድ ወስናችሁ እዚያ ለመቀመጥ ብትሄዱ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ የሚለውን ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ ግብጽ ወርዳችሁ በዚያ ለመኖር ብትወስኑ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስለ​ዚህ እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ግብ​ፅም ትገቡ ዘንድ በዚ​ያም ትቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ች​ሁን ብታ​ቀኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ግብጽ ትገቡ ዘንድ በዚያም ትቀመጡ ዘንድ ፊታችሁን ብታቀኑ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 42:15
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ኮበለለ፥ ተነሥቶም የኤፍራጥስን ወንዝ ተሻገረ፥ ፊቱንም ወደ ኮረብታማው አገር ገለዓድ አቀና።


ነገር ግን ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማያገለግለውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ያን ሕዝብ እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ።


ወደ ግብጽም ለመግባት በዚያም ለመቀመጥ ፊታቸውን ያቀኑ ሰዎች ሁሉ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታሉ፤ እኔም ከማመጣባቸው ክፉ ነገር ከእነርሱ አንድም ሰው በሕይወት አይተርፍም፥ አንድም ሰው አያመልጥም።


ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፦ “በግብጽ ምድር የምትገኙ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ስሙ።


ኢየሱስ የሚያርግበት ወራት በቀረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አቀና፤


ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች