Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 40:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የዘበኞቹም አለቃ ኤርምያስን ወሰደው እንዲህም አለው፦ “ጌታ አምላክህ ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተናገረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የዘበኞቹ አዛዥ ኤርምያስን ለብቻው ወስዶ፣ እንዲህ አለው፤ “አምላክህ እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህን ጥፋት ተናገረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የክብር ዘብ አዛዡ እኔን ገለል አድርጎ ለብቻ እንዲህ አለኝ፦ “አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን ምድር እንደሚያጠፋት አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ኤር​ም​ያ​ስን ወሰ​ደው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተና​ገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የዘበኞቹም አለቃ ኤርምያስን ወሰደው እንዲህም አለው፦ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተናገረ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 40:2
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለበዓልም በማጠናቸው አስቈጡኝ፥ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።


ያገኙአቸው ሁሉ አጠፉአቸው፥ ጠላቶቻቸውም፦ በጽድቅ ማደሪያ በጌታ ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በጌታ ላይ እነርሱ ኃጢአት ስለ ሠሩ እኛ አልበደልንም፥ አሉ።


የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ከአገሩ ድኆች ወይን ተካዮችና አራሾች እንዲሆኑ አስቀረ።


ጌታም እንዲህ አለ፦ “ነገር ግን እኔን ባትሰሙና እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥


“ነገር ግን ለጌታ ለእግዚአብሔር ባትታዘዝ በዛሬዋ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ሁሉ በጥንቃቄ ባትከተላቸው፥ እነዚህ ርግማኖች ሁሉ ይደርሱብሃል፤ ያጥለቀልቁሃልም፦


በዚያች ቀን እቀጣቸዋለሁ፤ እተዋቸዋለሁም፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያችም ቀን፥ ‘ይህ ጥፋት የደረሰብን፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን?’ ይላሉ።


“ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቆጡት ጌታ አይቶ ጣላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች