ኤርምያስ 40:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፦ “እባክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፥ የይሁዳም ትሩፍ እንዲጠፋ አንተን ለምን ይገድላል?” ብሎ በምጽጳ በድብቅ ለጎዶልያስ ተናገረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ “ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ሄጄ ልግደለው፤ ሸሽተው ወደ አንተ የመጡት አይሁድ እንዲበተኑ፣ በይሁዳም የቀሩት እንዲጠፉ ለምን ይገድልሃል?” ብሎ በምጽጳ ለጎዶልያስ በምስጢር ነገረው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ከዚህም በኋላ ዮሐናን በምጽጳ በግል እንዲህ አለው፦ “ይህን ያደረገ ማን እንደ ሆነ ሳይታወቅ ሄጄ እስማኤልን ልግደለው፤ እንዴት እርሱ አንተን ሊገድልህ ይደፍራል? እርሱ ከገደለህ እኮ በዙሪያህ ለተሰበሰቡት አይሁድ መበታተን ምክንያት ይሆናል፤ በይሁዳ ምድር ከምርኮ በቀሩትም ሕዝብ ላይ ታላቅ ጥፋትን ያመጣል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ “እባክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፥ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ነፍስህን ስለ ምን ይገድላል?” ብሎ በመሴፋ በቈይታ ለጎዶልያስ ተናገረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፦ እባክህ፥ ልሂድ፥ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፥ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ነፍስህን ስለ ምን ይገድላል? ብሎ በምጽጳ በቆይታ ለጎዶልያስ ተናገረ። ምዕራፉን ተመልከት |