Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 4:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ምድሪቱን አየሁ፥ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም አልነበረባቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ምድርን ተመለከትሁ፤ እነሆ ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች፤ ሰማያትንም አየሁ፣ ብርሃናቸው ጠፍቷል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ምድርን ተመለከትኩ፤ እነሆ ባድማ ሆናለች፤ ሰማይንም ተመለከትኩ፤ እነሆ ብርሃን አይታይበትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ምድ​ሪ​ቱን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ባዶ ነበ​ረች፤ ሰማ​ያ​ት​ንም ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ብር​ሃ​ንም አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ምድሪቱን አየሁ፥ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፥ ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም አልነበረባቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 4:23
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከነዚያ ቀናት መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይሎችም ይናወጣሉ።


የሰማይ ከዋክብትና ሠራዊታቸው፤ ብርሃን አይሰጡም፤ ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።


ምድርም ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።


“በዚያም ቀን፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ “ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለሁ፥ ቀኑም በብርሃን ሳለ ምድሩን አጨልማለሁ።


ምድሪቱም ከፊታቸው ትናወጣለች፥ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ።


በዚያን ቀን እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኹበታል፤ ማንም ወደ ምድር ቢመለከት፥ ጨለማንና መከራን ያያል፤ ብርሃን እንኳ በደመናዎች ይጋረዳል።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ታላቅና ነጭ ዙፋን፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


“ለተራሮች ልቅሶንና እንጉርጉሮን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው ባድማ ሆነዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፤ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።


ሰማያት ሆይ! በዚህ ተሣቀቁ፥ እጅግም ደንግጡና ተንቀጥቀጡ ይላል ጌታ።


ብርሃን ወደሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ።


በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ አይኖርም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች