Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 4:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነሆ፥ እንደ ደመና ይወጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ፤ ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እነሆ፤ እንደ ደመና ይንሰራፋል፤ ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣሉ፤ ፈረሶቹም ከንስር ይፈጥናሉ፤ መጥፋታችን ነውና ወዮልን!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “እነሆ የጠላት ሠራዊት እንደ ደመና አንዣቦአል፤ የጦር ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ፈጣኖች ናቸው፤ ፈረሶቹም ከንስር ይበልጥ ይበራሉ፤ ለእኛ ወዮልን! ጠፍተናል!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እነሆ! እንደ ደመና ይወ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ፈረ​ሶ​ቹም ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ናቸው። ተዋ​ር​ደ​ና​ልና ወዮ​ልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እነሆ፥ እንደ ደመና ይወጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ፥ ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 4:13
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳኦልና ዮናታን፥ የተዋደዱና የተስማሙ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ያልተለያዩ፤ ከንስርም ይልቅ የፈጠኑ፥ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።


ጌታና የቁጣው ጦር መሣሪያ፤ ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፤ ከሩቅ አገር፤ ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል።


ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።


ኢየሩሳሌም ተንገዳገዳለች፤ ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው ጌታን የሚቃወም፤ የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና።


ፍላጻቸው የተሳለ፤ ቀስታቸውም የተደገነ ነው፤ የሠረገሎቻቸውም መንኮራኩሮች እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው።


እነሆ፥ ጌታ መዓቱን በቁጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።


ስለ ስብራቴ ወዮልኝ! ቁስሌም የማይሽር ነው፥ እኔ ግን፦ “በእውነት የመከራ ቁስሌ ነው እርሱንም መሸከም ይገባኛል” አልሁ።


ስለ እኔ ጽኑ የሆነ ነፋስ ከእነዚህ ይመጣል ይባላል። አሁንም እኔ ደግሞ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።”


እንደታመመች የበኩርዋንም እንደምትወልድ ሴት የጭንቀት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ታቃስታለች፥ እጆችዋንም በመዘርጋት፦ “በነፍሰ ገዳዮች ፊት ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ!” አለች።


እኔ ሕያው በመሆኔ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ፥ በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፥ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፥ እንዲሁ በእውነት ይመጣል።


ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ እንደ ንስር ይበርራል ክንፉንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።


እነሆ፥ እንደ ንስር ወጥቶ ይበራል ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፥ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።”


ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፥ ምሕረትንም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል፥ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።”


በጽዮን፦ ‘እንዴት ተበዘበዝን! ምድሪቱንም ትተናልና፥ ቤቶቻችንንም አፍርሰዋልና እንዴት አብዝተን አፈርን!’ የሚል የልቅሶ ድምፅ ተሰምቶአል።”


ቆፍ። አሳዳጆቻችን ከሰማይ ንስር ይልቅ ፈጣኖች ሆኑ፥ በተራሮች ላይ አሳደዱን፥ በምድረ በዳ ሸመቁብን።


ከፈረሶቹ ብዛት የተነሣ አቧራቸው ይሸፍንሻል፤ ሰዎች ወደ ፈረስች ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ፥ ከፈረሰኞች፥ ከመንኩራኩሮች እና ከሰረገሎች ድምፅ የተነሣ ቅጥሮችሽ ይናወጣሉ።


አንተም ወደ ላይ ትወጣለህ፥ እንደ ማዕበል ትመጣለህ፤ አንተና ሠራዊትህ ሁሉ፥ ብዙ ሕዝብም ከአንተ ጋር ሆነው ምድርን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።


መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ፤ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና እንደ ንስር በጌታ ቤት ላይ እያንዣበበ ነው።


በዚያ ቀን ምሳሌ ይመስልባችኋል፥ በኀዘን እንጉርጉሮ ያለቅስላችኋል፤ እርሱም፦ “ፈጽመን ጠፍተናል፤ የሕዝቤን ድርሻ ቀየረ፤ ከእኔ እንዴት ወሰደው፤ እርሻችንን ለከዳተኞች ይከፋፍላል” ይላል።


ጌታ ለቁጣ የዘገየ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፤ ጌታ መንገዱ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።


ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኩላ ይልቅ አስፈሪዎች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፥ ለመንጠቅ እንደሚቸኩል ንስር ይበርራሉ።


ተመልሼም ዐይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ።


በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ በዚያን ጊዜም የምድር ነገዶች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤


ጌታ እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋው የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፥ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤


እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዐይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፤ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች