ኤርምያስ 36:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ይሁዲም ሦስት ወይም አራት ዓምድ ያኽል ባነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ ጸሐፊ በሚጠቀምበት ሰንጢ የተነበበለትን እየቀደደ ክርታሱ በሙሉ ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ይጥለው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ይሁዲ ከብራናው ሦስት ወይም አራት ዐምድ ባነበበ ቍጥር ንጉሡ ብራናው ሁሉ እስከሚያልቅ ድረስ በጸሓፊ ቢላዋ እየቈረጠ እንዲቃጠል ወደ እሳቱ ምድጃ ይጥል ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ይሁዲም ሦስት ወይም አራት ዐምድ ያኽል አንብቦ በጨረሰ ቊጥር ንጉሡ የተነበበለትን ብራና በመቊረጫ ቈራርጦ እሳት ውስጥ ይጥለው ነበር፤ በዚህም ዐይነት የብራናውን ጥቅል በሙሉ አቃጠለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ይሁዳም ሦስትና አራት ዐምድ ያህል በአነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ በብርዕ መቍረጫ ቀደደው፤ ክርታሱንም በምድጃ ውስጥ በአለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወደ አለው እሳት ጣለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ይሁዲም ሦስት ወይም አራት ዓምድ ያህል ባነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ በካራ ቀደደው፥ ክርታሱም በምድጃ ውስጥ ባለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ጣለው። ምዕራፉን ተመልከት |