ኤርምያስ 36:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ቃሎቹንም ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈርተው እርስ በእርሳቸው ተያዩ፥ ባሮክንም፦ “እነዚህን ቃላት ሁሉ በእርግጥ ለንጉሡ እንናገራለን” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 እነርሱም ቃሉን ሁሉ በሰሙ ጊዜ እርስ በርሳቸው በፍርሀት በመተያየት ባሮክን፣ “ይህን ሁሉ ቃል ለንጉሡ መንገር ይገባናል።” አሉት፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 አንብቦ ከጨረሰም በኋላ ከመደንገጣቸው የተነሣ እርስ በርሳቸው ተያይተው ባሮክን “ይህን ጉዳይ ለንጉሡ ማስታወቅ አለብን” አሉት፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እንዲህም ሆነ፦ ቃሉን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈርተው እርስ በርሳቸው ተመካከሩ፤ ባሮክንም፥ “ይህን ቃል ሁሉ በርግጥ ለንጉሡ እንናገራለን” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ቃሉንም ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈርተው እርስ በእርሳቸው ተመካከሩ፥ ባሮክንም፦ ይህን ቃል ሁሉ በእርግጥ ለንጉሡ እንናገራለን አሉት። ምዕራፉን ተመልከት |