ኤርምያስ 36:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 አለቆቹም ሁሉ፦ “በሕዝቡ ጆሮ ያነበብከውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና” የሚል መልእክት በኲሲ ልጅ በሰሌምያ ልጅ በናታንያ ልጅ በይሁዲ እጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ መጣ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 መኳንንቱ ሁሉ የኩሲን ልጅ የሰሌምያን ልጅ የናታንያን ልጅ ይሁዲን፣ “ለሕዝቡ ያነበብኸውን ብራና ይዘህ እንድትመጣ” ብለው ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ብራናውን ይዞ ወደ እነርሱ መጣ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ከዚህ በኋላ ባለ ሥልጣኖቹ ሁሉ ባሮክ ለሕዝቡ ያነበበውን የብራና ጥቅል ይዞ እንዲመጣ ይነግረው ዘንድ ይሁዲን ላኩ፤ (ይሁዲ የነታንያ ልጅ ሲሆን፥ ነታንያ የሸሌምያ ልጅ፥ ሸሌምያም የኩሺ ልጅ ነው፤) ባሮክም የብራናውን ጥቅል ይዞ ወደ እነርሱ መጣ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 አለቆቹም ሁሉ፥ “በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና” ብለው የኩሲ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የናታንያ ልጅ ይሁዳን ወደ ኔርዩ ልጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርዩም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ ወረደ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 አለቆቹም ሁሉ፦ በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና የሚል መልእክት በኵሲ ልጅ በሰሌምያ ልጅ በናታንያ ልጅ በይሁዲ እጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ መጣ። ምዕራፉን ተመልከት |