Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 34:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ቃል ኪዳኔንም የተላለፉትን ሰዎች፥ እንቦሳውንም ቈርጠው በቁራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳኑን ሕግጋት ያልፈጸሙትን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኪዳኔን ያፈረሱትንና በፊቴ የገቡትን የኪዳኑን ቃል ያልፈጸሙትን ሰዎች ሥጋውን ሁለት ቦታ ከፍለው በመካከሉ እንዳለፉት፣ እንደ እንቦሳው አደርጋቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ባሪያዎቻችሁን ነጻ ለማውጣት በፊቴ ቃል ኪዳን በገባችሁ ጊዜ አንድን ጥጃ በመቊረጥ ለሁለት ከፍላችሁ በመካከሉ አልፋችኋል፤ ነገር ግን እናንተ ያን ቃል ኪዳንና እኔም ከእስራኤል ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችኋል፤ ስለዚህ እናንተ በጥጃው ላይ እንዳደረጋችሁት እኔ በእናንተ ላይ አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ቃል ኪዳ​ኔን የተ​ላ​ለ​ፉ​ትን ሰዎች፥ በፊቴ ያደ​ረ​ጉ​ትን ቃል ኪዳን ያል​ፈ​ጸ​ሙ​ትን፥ እን​ቦ​ሳ​ው​ንም ቈር​ጠው በቍ​ራጩ መካ​ከል ያለ​ፉ​ትን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ቃል ኪዳኔንም የተላለፉትን ሰዎች፥ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳንን ቃል ያልፈጸሙትን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 34:18
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፥ ወፎችን ግን አልከፈለም።


አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንድወርሳት በምን አውቃለሁ? አለ።


የአሳፍ መዝሙር። የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት።


እነርሱ ግን በአዳም ቃል ኪዳንን ተላልፈዋል፤ በዚያም ቦታ እኔን አታለውኛል።


መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ፤ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና እንደ ንስር በጌታ ቤት ላይ እያንዣበበ ነው።


በራስ ወዳዶች፥ ለእውነት በማይታዘዙት ነገር ግን ለዐመፃ በሚታዘዙት ላይ ቁጣና መቅሠፍት ይመጣባቸዋል።


“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ አብሮህ የሚኖር ወንድ ወይም ሴት ኪዳኑን በማፍረስ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ሲፈጽም ቢገኝ፥


ጌታ አምላካችሁ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን ስታፈርሱ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ስታመልኩ፥ ስትሰግዱላቸውም፥ በዚያ ጊዜ የጌታ ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ከሰጣችሁም ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።”


እስራኤል ኃጢአት ሠርቶአል፤ ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል፤ እርም የሆነውንም ነገር ወሰዱ፥ ሰረቁም፥ ዋሹም፥ በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች