ኤርምያስ 34:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ፥ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ፥ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ፥ ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሰራዊቱ ሁሉ፣ በግዛቱም ሥር ያሉ መንግሥታትና ሕዝቦች ሁሉ ኢየሩሳሌምንና በአካባቢዋ የሚገኙትን ከተሞች ይወጉ በነበረ ጊዜ፣ እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ በግዛቱ ሥር ባሉት መንግሥታትና ሕዝቦች ጭምር እየተረዳ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ላይ የጦርነት አደጋ በሚጥልበት ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ፥ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ፥ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |