Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 33:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ ‘ለእስራኤል ቤትና ለይሁዳ ቤት የገባሁትን የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ተቃርቦአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “እነሆ ስለ እስ​ራ​ኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የሰ​ጠ​ሁ​ትን መል​ካም የተ​ስፋ ቃል የም​ፈ​ጽ​ም​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 33:14
31 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።


እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ “አዎን” ማለት የእርሱ ነው፤ ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር ክብር በእኛ ስለሚነገረው “አሜን” የምንለው እርሱ በኩል ነው።


“ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህችም ስፍራ እናንተን በመመለስ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።


በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ፥ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።


ቃሌን ሰምተሃልና፥ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ።”


“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤


ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክርነት ከሚጠብቁት ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባርያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክርነት የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።


ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው ፈለጉም መረመሩም፤


ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ፥ እግዚአብሔር ለእኛ የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበር።


እላችኋለሁና፥ እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት ሊያዩ ወደዱ አላዩምም፤ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወደዱ አልሰሙምም።”


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትደሰቱበትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ከዚህ በኋላ የቀሩት ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።


ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።


“የእስራኤልን ቤትና የይሁዳን ቤት በሰው ዘርና በእንስሳ ዘር የማራባበት ዘመን፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እንዳመጣሁ፥ እንዲሁ ለእነርሱ የተናገርሁትን በጎነት ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።


የምሠራላቸውንም በጎነት ሁሉ በሚሰሙ የምድር አሕዛብ ሁሉ ፊት ይህች ከተማ ለእኔ የምስጋናና የክብር የደስታም ስም ትሆናለች፤ እኔም ስላደረግሁላት በጎነትና ሰላም ሁሉ ይፈራሉ ይንቀጠቀጣሉም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች