Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 32:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ባለማቋረጥ ባስተምራቸውም እንኳ ተግሣጽን ለመቀበል አልሰሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፤ ደጋግሜ ባስተምራቸውም አይሰሙም፤ ተግሣጽም አይቀበሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እነርሱ እኔን ትተው ሄደዋል፤ ዘወትር በመደጋገም ባስተምራቸውም አልሰሙኝም፤ ተግሣጼንም አልተቀበሉም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ፊታ​ቸ​ው​ንም ሳይ​ሆን ጀር​ባ​ቸ​ውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማ​ለዳ ተነ​ሥቼ ሳስ​ተ​ም​ራ​ቸው ተግ​ሣ​ጽን ይቀ​በሉ ዘንድ አል​ሰ​ሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ፥ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ሳስተምራቸው ተግሣጽን ይቀበሉ ዘንድ አልሰሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 32:33
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጠላት ፊት እንደ ምሥራቅ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፥ በጥፋታቸውም ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”


ግንዱን፦ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ ድንጋዩንም፦ ‘አንቺ ወለድሺኝ’ ይላሉ፤ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፥ በመከራቸው ጊዜ ግን፦ ‘ተነሥተህ አድነን’ ይላሉ።


ያልሰማችሁትን በማለዳ ተነሥቼ ወደ እናንተ የላክኋቸውን የባርያዎቼን የነቢያትን ቃላት ባትሰሙ፥


“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሂድና ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለተቀመጡ ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ቃሎቼን ለመስማት ተግሣጽን አትቀበሉምን? ይላል ጌታ።


እንዲሁም፦ ‘እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ሥራችሁንም አሳምሩ፥ ልታገለግሉአቸውም ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ’ እያልሁ በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ላክሁባችሁ፤ ላክሁ፥ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም እኔንም አልሰማችሁኝም።


ሆኖም በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ እንዲህ ብዬ ላክሁባችሁ፦ ‘እባካችሁ፥ እንደዚህ ያለ የጠላሁትን ርኩስ ነገር አታድርጉ።’


አሁንም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስላደረጋችሁ፥ ይላል ጌታ፥ በማለዳም ተነሥቼ ባለማቋረጥ በተናገርኋችሁ ጊዜ ስላልሰማችሁ፥ በጠራኋችሁም ጊዜ ስላልመለሳችሁ፥


ነገር ግን በክፉ ልባቸው ሐሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደፊትም ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።


አንተም፦ “የአምላኩን የጌታን ድምፅ ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ታጥቶአል።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለረሳሽኝ፥ ወደ ኋላሽም ስለጣልሽኝ፥ አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ግልሙትናሽን ተሸከሚ።


ወደ ጌታ ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በጌታ መቅደስ መግቢያ፥ በመተላለፊያውና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት ያህል ሰዎች ነበሩ፥ ጀርባቸው ወደ ጌታ መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፥ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።


አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከእኔ ዘንድ ራቁ፤ ለበኣሊምም ይሠው ነበር፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥኑ ነበር።


እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ በእልኸኝነት ጀርባቸውን አዞሩ፤ ጆሮአቸውንም ደፈኑ።


ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች