ኤርምያስ 32:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ምንም እንኳ ከተማይቱ ለከለዳውያን እጅ ተላልፋ ብትሰጥም፤ አቤቱ ጌታ ሆይ! አንተ ግን፦ “እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ” አልኸኝ።’ ” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከተማዪቱ ለባቢሎናውያን ዐልፋ እየተሰጠች፣ ‘መሬቱን በብር ግዛ፤ ግዥውንም በምስክሮች ፊት ፈጽም’ ትለኛለህ።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ከተማይቱ በባቢሎናውያን ልትያዝ ተቃርባ ሳለ መሬቱን በምስክሮች ፊት እንድገዛ ያዘዝከኝ አንተ ነህ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 አንተም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እርሻውን በብር ግዛ፤ ምስክሮችንም ጥራ አልኸኝ፤ እኔም ውሉን ጽፌ አተምሁ፤ ምስክሮችንም አቆምሁ፤ ከተማዪቱ ግን ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 አንተም፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ አልኸኝ፥ ከተማይቱ ግን ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች። ምዕራፉን ተመልከት |