ኤርምያስ 31:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 የሬሳና የአመድ ሸለቆ ሁሉ፥ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ ያለው የትልም እርሻ ሁሉ፥ በምሥራቅም በኩል እስካለው እስከ ፈረሰ በር ማዕዘን ድርስ ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ወዲህ ለዘለዓለም አይነቀልም አይፈርስምም።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ሬሳና ዐመድ የሚጣልበት ሸለቆ በሙሉ፣ በምሥራቅ በኩል የቄድሮንን ሸለቆ ይዞ እስከ ፈረስ በር የሚደርሰው ደልዳላ ቦታ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ከተማዪቱ አትነቀልም፤ አትፈርስምም።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 በድንና ዐመድ የሚጣልበት መላው ሸለቆ በምሥራቅ በኩል እስከ ፈረስ በር ድረስ እንኳ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከተማይቱም እንደገና ከቶ አትፈርስም፤ አትደመሰስምም።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 የአስሬሞትም ሸለቆ ሁሉ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረስ በር ማዕዘን ድረስ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ወዲህ ለዘለዓለም አይነቀልም፤ አይፈርስምም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 የሬሳም ሸለቆ ሁሉ የአመድም እርሻ ሁሉ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረሰ በር ማዕዘን ድረስ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፥ ከእንግዲህም ወዲህ ለዘላለም አይነቀልም አይፈርስምም። ምዕራፉን ተመልከት |