Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 31:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በዚያን ጊዜም ድንግሊቱ በሽብሸባ ትደሰታለች፥ ጉልማሶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እለውጣለሁ፥ አጽናናቸዋለሁም፥ ከኀዘናቸውም ደስ አሰኛቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ኰረዶች ይዘፍናሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤ ጐረምሶችና ሽማግሌዎችም ይፈነጥዛሉ፤ ልቅሷቸውን ወደ ደስታ እለውጣለሁ፤ ከሐዘናቸውም አጽናናቸዋለሁ፤ ደስታንም እሰጣቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ልጃገረዶቻቸውም በደስታ ይጨፍራሉ፤ ወንዶች ወጣቶችና ሽማግሌዎችም ደስ ይላቸዋል፤ አጽናናቸዋለሁ፤ ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፥ ሐዘናቸውንም ወደ ሐሴት እለውጣለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በዚ​ያን ጊዜም ደና​ግሉ በዘ​ፈን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቱና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም በአ​ንድ ላይ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ እኔም ልቅ​ሶ​አ​ቸ​ውን ወደ ደስታ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከኀ​ዘ​ና​ቸ​ውም ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በዚያን ጊዜም ድንግሊቱ በዘፈን ደስ ይላታል፥ ጐበዛዝቱና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ደስ ይላቸዋል፥ ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እመልሳለሁ፥ አጽናናቸውማለሁ፥ ከኅዘናቸውም ደስ አሰኛቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 31:13
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ሰማ ማረኝም፥ ጌታ ረዳቴ ሆነኝ።


ጌታ ለክብሩ የተከላቸው ጽድቃዊ የባሉጥ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች በአመድ ፋንታ አክሊልን እንዳደርግላቸው፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘን መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እንድሰጣቸው ልኮኛል።


ጌታ የተቤዣቸው ይመለሳሉ ወደ ጽዮንም ይመጣሉ፤ የዘለዓለምም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ልቅሶም ይሸሻል።


የእስራኤል ድንግል ሆይ! እንደገና እሠራሻለሁ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ሐሤት በሚያደርጉ ዘፋኞች ሽብሸባ እያሸበሸብሽ ትወጫለሽ።


እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደገና አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።


ጌታም ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርሷም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፤ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔድን በረሀዋንም እንደ ጌታ ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።


ጌታም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፥ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላላም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።


ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።


እግዚአብሔር በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ።


የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ምረቃውን በደስታ፥ በምስጋና፥ በመዝሙር፥ በጸናጽል፥ በበገናና በክራር ለማክበር ሌዋውያኑን ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በየሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ፈለጉ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም፥ የአምስተኛው፥ የሰባተኛው፥ የአሥረኛው ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ፥ የሐሤትም በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ!


ጌታ የዘለዓለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም፥ ጨረቃሽም አትገባም።


ጌታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና፥ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤትም ለመሥራት እጃቸውን እንዲያጸኑ የአሦርን ንጉሥ ልብ ወደ እነርሱ መልሶአልና የቂጣውን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አከበሩ።


አድፍጣችሁ ተጠባበቁ። የሴሎ ልጃገረዶች ለጭፈራ ወደዚያ በሚወጡበት ጊዜ፥ ከወይኑ አትክልት ቦታ ወጥታችሁ ከልጃገረዶቹ ለየራሳችሁ ሚስት ጥለፉ፤ ወደ ብንያምም ምድር ሂዱ።


የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት፥ አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እንዳውጅ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ እንዳጽናና፥


በዕንባ የሚዘሩ በእልልታ ይለቅማሉ።


ጉልማሶችና ልጃገረዶች፥ ሽማግሌዎችና ልጆች፥


በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ከቁጣህ ተመለስህ፤ ደግሞም አጽናንተኸኛልና እወድስሃለሁ።


እርሱም፦ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የሙሽራው ድምፅና የሙሽራይቱ ድምፅ፥ ወደ ጌታም ቤት፦ ‘ጌታ ቸር ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታን አመስግኑ!’ እያሉ የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ ነው። የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል ጌታ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች