Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 31:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አሕዛብ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውጁ፦ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል” በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ሕዝቦች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ሩቅ ባሉ የባሕር ጠረፎችም፣ ‘እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፤ መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል’ ብላችሁ ዐውጁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሕ​ዛብ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በሩ​ቅም ላሉ ደሴ​ቶች አው​ሩና፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የበ​ተነ እርሱ ይሰ​በ​ስ​በ​ዋል፤ እረ​ኛም መን​ጋ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሕዛብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፦ እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 31:10
43 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።


እረኛ በተበተኑት መንጋዎቹ መካከል ሳለ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በጨለማ ቀን፥ ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ።


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።


የፈለስክበት ስፍራ ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ቢሆን እንኳ፥ ጌታ እግዚአብሔር ከዚያ ይሰበስብሃል፤ ከዚያም መልሶ ያመጣሃል።


ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፤ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ።


በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ ይከተሉኝማል፤


እነሆ በዚያ ዘመን፥ ያስጨነቁሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ አንካሳይቱንም አድናለሁ፥ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፤ ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ።


“አንተ ታናሽ መንጋ! መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።


በዚያም ቀን አምላካቸው ጌታ ሕዝቡን እንደ መንጋ ያድናቸዋል፤ እነርሱም ለአክሊል እንደሚሆኑ እንደ ከበሩ ድንጋዮች ይሆናሉ፥ በምድሩም ላይ ያበራሉ።


ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


ይህም ሰላም ይሆናል፤ አሦር ወደ ምድራችን ከመጣ፥ ምሽጎቻችንንም ከረገጠ፥ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።


በዚያ ቀን ይላል ጌታ፥ አንካሳይቱን እሰበስባለሁ፥ የተጣለችውንና የጎዳኋትን አከማቻለሁ፤


ያዕቆብ ሆይ፥ ሁላችሁንም ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልን ትሩፍ በአንድ ላይ እሰበስባለሁ፤ በጋጣ ውስጥ እንዳሉ በጎች፥ በማሰማርያው ውስጥ እንዳለ መንጋ አደርገዋለሁ፤ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።


አገልጋዬ ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል፤ በፍርዴ ይሄዳሉ፥ ትእዛዜን ይጠብቃሉ ይፈጽሟቸዋልም።


ከአሕዛብም ዘንድ አወጣችኋለሁ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እሰበስባችኋለሁ።


ስለዚህ እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል አርቄ ብወስዳቸውም፥ በአገሮች መካከል ብበትናቸውም፥ በሄዱባቸው አገሮች በዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ።


ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፥ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፥ ፍርድንም አደርግብሻለሁ፥ ከአንቺም የተረፉትንም ሁሉ ወደ ሁሉም ነፋሳት እበትናለሁ።


የመከበብም ወራት ሲፈጸም አንድ ሦስተኛውን በከተማይቱ መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወስደህ ዙሪያውን በሰይፍ ትመታዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፥ እኔም ከኋላቸው ሰይፍ እመዝዛለሁ።


እስራኤልንም ወደ ማሰማርያው እመልሳለሁ፥ በቀርሜሎስና በባሳንም ላይ ይሰማራል፥ ሆዱም በኤፍሬም ተራራና በገለዓድ ላይ ትጠግባለች።


እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።


የጤሮስን ነገሥታትም ሁሉ፥ የሲዶናን ነገሥታትም ሁሉ፥ በባሕር ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትንም፥


እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለጌታ ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ፥ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ለማምጣት፥ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።


ጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፥ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ።


ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርሷም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ፥ ለጌታ አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።


በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ያበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።


ደሴቶች ሆይ፥ በፊቴ ዝም በሉ፤ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፤ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፤ ለፍርድ በአንድነት እንቅረብ።


በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ጌታ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።


እነዚህ ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ እልልም ይላሉ፥ ስለ ጌታ ክብርም ከባሕር ይጣራሉ።


የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፥ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ።


ፈጽሜ እበትናቸዋለሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ፤’ አልኩ።


ከእነዚህም በባሕር ዳርቻ ሕዝቦች፥ ሁሉም በየምድራቸው፥ በየቋንቋቸው፥ በየነገዳቸው፥ በየሕዝባቸው ተከፋፍለው የሚኖሩ የያፌት ልጆች ዘር ናቸው።


እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም ባድማ ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ይፈርሳሉ።


የዳዊት መዝሙር። ጌታ እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።


የበጎችህን ሁኔታ አስተውለህ እወቅ፥ በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር፥


አጽናኑ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ።


ከባቢሎን ውጡ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፥ ይህንንም ንገሩ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩ፦ “ጌታ ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል!” በሉ።


እንደ ልቤም የሆኑ እረኞችን እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ያሰማርዋችኋል።


የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፥ ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነርሱም አንድም አይጐድልም፥ ይላል ጌታ።


እኔም፦ “አንተ ወዴት ነው የምትሄደው?” አልኩት። እርሱም፦ “ኢየሩሳሌምን ልለካትና ወርድና ርዝመቷ ስንት መሆኑን ለማየት ነው የምሄደው” አለኝ።


ጌታ ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።


በፉጨት እጠራቸዋለሁ፤ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስለምቤዣቸው እንደ ቀድሞው ብዙ እጥፍ ይሆናሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች