ኤርምያስ 30:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ጠይቁ፥ ወንድ ይወልድ እንደሆነ ተመልከቱ፤ ስለምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ ሴት እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ ፊቱም ሁሉ ገርጥቶ አየሁ? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እስኪ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤ ወንድ መውለድ ይችላል? ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣ የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ! ወንድ አምጦ ልጅን መውለድ ይችላልን? ታዲያ ወንድ ሁሉ እንደ ወላድ ሴት በእጆቹ ወገቡን ይዞ የማየው ስለምንድን ነው? የእያንዳንዱስ ሰው ፊት ስለምን ገረጣ? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ጠይቁ፤ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍረት ተለውጦ አየሁ? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ጠይቁ፥ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ፥ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቁረት ተለውጦ አየሁ? ምዕራፉን ተመልከት |