ኤርምያስ 30:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 እነሆ፥ የጌታ ዐውሎ ነፋስ! ቁጣው ወጥቶአል፥ ጥቅል ዐውሎ ነፍስ፤ እርሱም በክፉዎች ራስ ላይ ይወርዳል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 እነሆ፤ የእግዚአብሔር ማዕበል፣ በቍጣ ይነሣል፤ የሚገለባብጥም ዐውሎ ነፋስ፣ በክፉዎች ዐናት ላይ ይወርዳል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለው የእግዚአብሔር ቊጣ እንደ ኀይለኛ ነፋስ እየተገለባበጠ በክፉዎች ራስ ላይ ይወርዳል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 እነሆ የእግዚአብሔር ቍጣ ለመቅሠፍት ወጥቶአል፤ የመዓቱንም ጥፋት በኃጥኣን ራስ ላይ አምጥቶአል፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፥ እርሱም ቍጣው፥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፋስ ወጥቶአል፥ የዓመፀኞችንም ራስ ይገለባብጣል። ምዕራፉን ተመልከት |