Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 30:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ልጆቻቸውም እንደ ቀድሞ ይሆናሉ፥ ማኅበራቸውም በፊቴ ጸንቶ ይኖራል፤ የሚያስጨንቋቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ልጆቻቸው እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤ ማኅበረ ሰቡም በፊቴ የጸና ይሆናል፤ የሚጨቍኗቸውን ሁሉ እቀጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ልጆቻቸው እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ተፈርተው ይኖራሉ፤ ይህም ማኅበራዊ ኑሮአቸው በፊቴ የጸና ይሆናል፤ ሲጨቊኑአቸው የነበሩትንም ሁሉ እቀጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ልጆ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ቀድ​ሞው ይሆ​ናሉ፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም በፊቴ ጸንቶ ይኖ​ራል፤ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸ​ው​ንም ሁሉ እቀ​ጣ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ልጆቻቸውም እንደ ቀድሞ ይሆናሉ፥ ማኅበራቸውም በፊቴ ጸንቶ ይኖራል፥ የሚያስጨንቋቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 30:20
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም።


አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።


አስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን አስበላቸዋለሁ፥ እንደ ጣፋጭም ወይን ጠጅ ደማቸውን ጠጥተው ይሠክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ ጌታ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብ ኃያል እንደሆንሁ ያውቃል።


ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቁጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።


በጽድቅ ትታነጺያለሽ፤ ከግፍ ራቂ፥ አትፈሪምም፥ ድንጋጤም ወደ አንቺ አይቀርብም።


እስራኤል ለጌታ ቅዱስ ነበረ፥ የአዝመራውም በኵራት ነበረ፤ የበሉት ሁሉ እንደ በደለኞች ይቈጠራሉ፥ ክፉም ነገር ይመጣባቸዋል፥ ይላል ጌታ።”


ስለዚህ የሚውጡህ ሁሉ ይዋጣሉ፥ ጠላቶችህም ሁሉ አንድም ሳይቀሩ ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፥ የበዘበዙህንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ።


እኔን ለዘለዓለም በመፍራት ለእነርሱም ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም እንዲሆንላቸው አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።


አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፥ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።


የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ ስለምራራላቸው ወደ ቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው ጌታ ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁ።


በፉጨት እጠራቸዋለሁ፤ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስለምቤዣቸው እንደ ቀድሞው ብዙ እጥፍ ይሆናሉ።


የከተማይቱም አደባባዮች በጎዳናው ላይ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች