ኤርምያስ 29:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ይህም የሆነው ቃሎቼን ስላልሰሙ ነው፥ ይላል ጌታ፤ በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ በተደጋጋሚ ላኩኝ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፥ ይላል ጌታ።’ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ደጋግሜ የላክሁላቸውን ቃሌን አልሰሙምና” ይላል እግዚአብሔር፤ “እናንተ ምርኮኞችም አልሰማችሁም” ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ይህም ሁሉ የሚደርስባቸው በአገልጋዮቼ በነቢያት አማካይነት በመደጋገም የላክሁላቸውን ቃሌን ካለመስማትና ካለመታዘዝ የተነሣ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ይህም የሆነው ቃሌን ስላልሰሙ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በማለዳ ባሪያዎችን ነቢያትን ወደ እነርሱ ሰድጃለሁና፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፤ ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ይህም የሆነው ቃሌን ስላልሰሙ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ ሰድጃለሁና፥ እናንተ ግን አልሰማችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከት |