ኤርምያስ 27:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ነገር ግን ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማያገለግለውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ያን ሕዝብ እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 “ ‘ “ነገር ግን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር የማይገዛ፣ ዐንገቱንም ከቀንበሩ በታች ዝቅ የማያደርግ ማንኛውንም ሕዝብ ወይም መንግሥት በእጁ እስከማጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፣ በመቅሠፍትም እቀጣዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 “ነገር ግን ማንኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት ‘እርሱን አላገለግልም፤ በቀንበሩም ሥር ሆኜ አልገዛም’ ቢል ናቡከደነፆር ራሱ እንዲደመስሰው እስከ ፈቀድኩለት ድረስ፥ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲቀጡ አደርጋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 “ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከንደነፆር የማይገዛውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማይገዛውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከት |