ኤርምያስ 26:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ንጉሡም ኢዮአቄም ኃያላኑም ሁሉ አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ፈለገ፤ ኦርዮም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ ወደ ግብጽም ገባ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ንጉሥ ኢዮአቄም፣ የጦር አለቆቹና ባለሥልጣኖቹ ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ንጉሡ ሊገድለው ፈለገ፤ ኦርዮም ይህን ሰምቶ በፍርሀት ወደ ግብጽ ሸሸ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ንጉሥ ኢዮአቄምና መኳንንቱ፥ እንዲሁም የጦር አዛዦቹ ኡሪያ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ፥ ኡሪያ እንዲገደል ንጉሡ ፈለገ፤ ኡሪያ ግን ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ ወደ ግብጽም ሸሽቶ አመለጠ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ንጉሡም ኢዮአቄም፥ ሠራዊቱ ሁሉ፥ አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ፈለገ፤ ኡርያም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ፤ ወደ ግብፅም ገባ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ንጉሡም ኢዮአቄም ኃያላኑም ሁሉ አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ፈለገ፥ ኦርዮም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ ወደ ግብጽም ገባ። ምዕራፉን ተመልከት |