Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 26:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፦ “በአምላካችን በጌታ ስም ስለ ተናገረን ይህ ሰው ሞት አይገባውም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ባለሥልጣኖቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፣ “ይህ ሰው በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ተናግሯልና ሊገደል አይገባውም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህ በኋላ መሪዎቹና ሕዝቡ፦ “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ስለ ሆነ ሞት አይገባውም” ሲሉ ለካህናቱና ለነቢያቱ ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ለካ​ህ​ና​ትና ለነ​ቢ​ያተ ሐሰት፥ “ይህ ሰው በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተና​ግ​ሮ​ና​ልና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፦ ይህ ሰው በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ተናግሮናልና ሞት አይገባውም አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 26:16
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሕጋቸውም ስለ መከራከር እንደ ከሰሱት አገኘሁ እንጂ ለሞት ወይም ለእስራት የሚያደርስ ክስ አይደለም።


ታላቅ ጩኸትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑት ጻፎች ተነሥተው “በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይስ መልአክ ተናግሮት ይሆን?” ብለው ተከራከሩ።


እኔ ግን ሞት የሚገባውን ነገር እንዳላደረገ አስተዋልሁ፤ እርሱም ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ እሰደው ዘንድ ቆረጥሁ።


ነገር ግን ኤልናታንና ድላያ ገማርያም ክርታሱን እንዳያቃጥል ንጉሡን ቢለምኑትም እንኳ፥ እርሱ ግን አልሰማቸውም።


አለቆቹም ባሮክን፦ “አንተና ኤርምያስ ሂዱ፥ ተሸሸጉ፥ ወዴትም እንደ ሆናችሁ ማንም ሰው አይወቅ” አሉት።


የመቶ አለቃውም የሆነውን ነገር ባየ ጊዜ “ይህ ሰው በእውነት ጻድቅ ነበረ፤” ብሎ እግዚአብሔርን አከበረ።


እኛ ስለ አደረግነው የሚገባንን እየተቀበልን ነው፤ በእኛ ላይ የተወሰነው ትክክለኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም ክፋት አልሠራም፤” ብሎ ገሠጸው።


የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር” አሉ።


ካህናቱና ነቢያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፦ “በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁት በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሯልና ይህ ሰው ሞት ይገባዋል” ብለው ተናገሩ።


የሰው አካሄድ ጌታን ደስ ያሰኘው እንደሆነ፥ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል።


ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰምተው ማንም ሰው ወንድ ባርያውንና ሴት ባርያውን አርነት እንዲያወጣ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ማንም እንዳይገዛቸው አደረጉ፤ እነርሱም ሰምተው አርነት አወጡአቸው።


አለቆችም ተቈጥተው ኤርምያስን መቱት፥ የጸሐፊውንም የዮናታንን ቤት የእስር ቤት አድርገውት ነበርና በዚያ ቤት አስረው አኖሩት።


በክፉዎች ላይ ለእኔ የሚነሣ ማን ነው? ዓመፅንስ በሚያደርጉ ላይ ለእኔ የሚከራከር ማን ነው?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች