ኤርምያስ 26:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 የይሁዳም አለቆች እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ ከንጉሥ ቤት ወደ ጌታ ቤት ወጡ፥ በአዲሱም በጌታ ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 የይሁዳም ባለሥልጣኖች ስለ እነዚህ ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ ከቤተ መንግሥት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በእግዚአብሔር ቤት፣ አዲሱ በር በተባለው መግቢያ ተቀመጡ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 የይሁዳ መሪዎችም የሆነውን ነገር በሰሙ ጊዜ ከቤተ መንግሥት ወጥተው ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ በቤተ መቅደሱም በአዲሱ የቅጽር በር ስፍራቸውን ያዙ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 የይሁዳም አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከንጉሡ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 የይሁዳም አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከንጉሥ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፥ በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ። ምዕራፉን ተመልከት |