Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 25:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ቃሎቼን አልሰማችሁምና

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ቃሌን ስላልሰማችሁ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “አናዳምጥም ከማለታችሁም የተነሣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ስለ​ዚህ ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቃሌን አልሰማችሁምና እነሆ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 25:8
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ጌታም እንዲመልሱአቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፥ እነርሱ ግን አላደመጡም።


ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ለመሄድ ያልወደዱት፥ ለሕጉም ያልታዘዙለት ጌታ እርሱ አይደለምን?


“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።”


በደኅንነትሽ ጊዜ ተናገርሁሽ፤ አንቺም፦ ‘አልሰማም’ አልሽ። ከሕፃንነትሽ ጀምሮ ድምፄን አለመስማትሽ መንገድሽ ነው።


ለእናንተ ጉዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ አስቆጣችሁኝ እንጂ አልሰማችሁኝም፥ ይላል ጌታ።


እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


ይህም የሆነው ቃሎቼን ስላልሰሙ ነው፥ ይላል ጌታ፤ በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ በተደጋጋሚ ላኩኝ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፥ ይላል ጌታ።’


የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤’” እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል ጌታ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች