Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 22:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ‘ለራሴ ሰፊ ቤት ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ’ ለሚል፥ መስኮቶችንም ለሚያወጣለት፥ በዝግባም ሥራ ለሚያስጌጠው፥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ‘ባለትልልቅ ሰገነት፣ ሰፊ ቤተ መንግሥት ለራሴ እሠራለሁ’ ለሚል ወዮለት! ሰፋፊ መስኮቶችን ያበጅለታል፤ በዝግባ ዕንጨት ያስጌጠዋል፤ ቀይ ቀለምም ይቀባዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ይህ ሰው “ለራሴ ትልቅ ቤት ከሰፊ ሰገነት ጋር እሠራለሁ፤ እንዲሁም ሰፋፊ መስኮቶችን አወጣለታለሁ፤ ቤቱን በሰፋፊ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስጌጠዋለሁ፤ ደማቅ ቀይ ቀለምም እቀባዋለሁ” ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “ለራሴ ሰፊ ቤት፥ ትል​ቅም ሰገ​ነት እሠ​ራ​ለሁ ለሚል፥ መስ​ኮ​ት​ንም ለሚ​ያ​ወጣ፥ በዝ​ግ​ባም ሥራ ለሚ​ያ​ስ​ጌጥ፥ በቀይ ቀለ​ምም ለሚ​ቀ​ባው ወዮ​ለት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ለራሴ ሰፊ ቤት ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፥ መስኮትንም ለሚያወጣ፥ በዝግባም ሥራ ለሚያሳጌጥ፥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 22:14
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነቢዩን ናታንን፥ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።


ታላቁንም ቤት በጥድ እንጨት ከደነው፥ በጥሩም ወርቅ ለበጠው፤ የዘንባባና የሰንሰለት አምሳል ቀረጸበት።


ዓመፃን የሚወድድ ክርክርን ይወድዳል፥ ደጁንም ዘለግ የሚያደርግ ውድቀትን ይሻል።


ሥራህን በውጭ አሰናዳ፥ ለራስህ በእርሻ ውስጥ አዘጋጀው፥ ከዚያም በኋላ ቤትህን ሥራ።


የቤታችን ሠረገላ የዝግባ ዛፍ ነው፥ የጣሪያችንም ማዋቀሪያ የጥድ ዛፍ ነው።


ጡቦቹ ወድቀዋል፤ እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤ የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤ እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።


አመንዝራነቷን ቀጠለችበት፤ በቀይ ቀለም የተሳለ የከለዳውያን ስዕል፥ በግድግዳ ላይ የተቀረጸ የወንዶች ምስል አየች።


ጌታ እግዚአብሔር፦ “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ጠልቻለሁ፤ ስለዚህ ከተማይቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአል፥ ይላል ጌታ የሠራዊት አምላክ።


ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በታጠሩ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?


ኤዶም፦ “እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን” ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ የክፋት አገር፥ ጌታ ለዘለዓለም የተቆጣው ሕዝብ ብለው ይጠሩአቸዋል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች