ኤርምያስ 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ካህናቱም፦ ‘ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም፥ የሕግ አዋቂዎች አላወቁኝም፤ ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበዓል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባውንም ነገር ተከተሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ‘እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው ካህናቱ አልጠየቁም፤ ከሕጉ ጋራ የሚውሉት አላወቁኝም፤ መሪዎቹ ዐመፁብኝ፤ ነቢያቱም በበኣል ስም ተነበዩ፤ ከንቱ ነገሮችን ተከተሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ካህናቱ ‘እግዚአብሔር ወዴት አለ?’ ብለው አልጠየቁም፤ የሕግ ምሁራን እንኳ አላወቁኝም፤ የሕዝብ ገዢዎች በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ነቢያትም በበዓል ስም ትንቢት ተናገሩ፤ ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችንም አመለኩ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ካህናቱም፦ እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፤ ሕጌን የተማሩትም አላወቁኝም፤ ጠባቂዎችም ዐመፁብኝ፤ ነቢያትም በበዐል ትንቢት ተናገሩ፤ የማይጠቅማቸውንም ነገር ተከተሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ካህናቱም፦ እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም፥ ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበኣል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባንም ነገር ተከተሉ። ምዕራፉን ተመልከት |