ኤርምያስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እነርሱም፦ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳም በባድማ ጉድጓድም ባለበት ምድር፥ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እነርሱም፣ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፣ በወና ምድረ በዳ፣ በጐድጓዳና በበረሓ መሬት፣ በደረቅና በጨለማ ቦታ፣ ሰው በማያልፍበትና በማይኖርበት ስፍራ የመራን እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው አልጠየቁም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እኔ እነርሱን ከምድረ ግብጽ አወጣኋቸው፤ በምድረ በዳ መራኋቸው፤ ጐድጓዳማ በሆነ መንገድ ድርቅና ጨለማ በበዛበት በረሓ፥ ማንም በማይኖርበትና በማይመላለስበት ምድር አሳለፍኳቸው፤ እነርሱ ግን ‘ይህን ሁሉ ያደረገልን አምላክ ወዴት ነው?’ ብለው እንኳ አልጠየቁም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እነርሱም፥ “ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳና በባድማ፥ ዕንጨትና ውኃ፥ የእንጨት ፍሬም በሌለበት ምድር፥ ሰው በማያልፍበትና የሰው ልጅም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እነርሱም፦ ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳም በባድማ ጕድጓድም ባለበት ምድር፥ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም። ምዕራፉን ተመልከት |