ኤርምያስ 2:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)37 ከዚያ ደግሞ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ትወጫለሽ፥ ምክንያቱም ጌታ የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽም።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም37 የታመንሽባቸውን እግዚአብሔር ስላዋረደ፣ በእነርሱም ስለማይከናወንልሽ፣ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያም ትወጫለሽ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም37 እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ በዕፍረት ከዚያ ቦታ ትሄጂአለሽ፤ እኔ እግዚአብሔር አንቺ የምትታመኝባቸውን ሁሉ ስላስወገድኩ ከእነርሱ የምታገኚው ምንም ነገር አይኖርም።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)37 እግዚአብሔርም ተስፋሽን አስቈርጦሻልና፥ በእርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)37 እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ። ምዕራፉን ተመልከት |