Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 2:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 አንቺ ግን፦ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በእውነት ቁጣው ከእኔ ተመልሶአል’ አልሽ። እነሆ፦ ‘ኃጢአት አልሠራሁም’ ብለሻልና በፍርድ እከስሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በርግጥ ቍጣው ከእኔ ርቋል’ ትያለሽ። እኔ ግን እፈርድብሻለሁ፤ ‘ኀጢአት አልሠራሁም’ ብለሻልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፤ በእ​ው​ነት ቍጣው ከእኔ ይመ​ለስ አልሽ። እነሆ ኀጢ​አት አል​ሠ​ራ​ሁም ብለ​ሻ​ልና እፋ​ረ​ድ​ሻ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፥ በእውነት ቍጣው ከእኔ ተመልሶአል አልሽ። እነሆ፦ ኃጢአት አልሠራሁም ብለሻልና በፍርድ እከስስሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 2:35
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

‘እኔ ንጹሕ ነኝ፥ በደል የለብኝም፤ ያለ እንከን ነኝ፥ ኃጢአትም የለብኝም፥


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


“ስለምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።


“ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃላት ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ‘ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገርን ለምን ጌታ ተናገረብን? በደላችንስ ምንድነው? በአምላካችንስ በጌታ ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድነው?’ ቢሉህ፥


አንቺስ፦ ‘ራሴን አላረከስኩም በዓሊምንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ምን እንዳደረግሽም እወቂ፤ በመንገዶችዋ ላይ ወድያና ወዲህ የምትቅበዘበዥ ወጣት ግመል ሆነሻል፤


“ከእኔ ጋር የምትከራከሩት ለምንድን ነው? ሁላችሁ ዐምፃችሁብኛል ይላል ጌታ።


“ስለዚህ ከእናንተ ጋር ገና እከራከራለሁ፥ ይላል ጌታ፥ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ።


ጌታ ከአሕዛብ ጋር ሙግት አለውና ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል ጌታ።


መረቤን በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ባቢሎንም አመጣዋለሁ፥ በዚያም በእኔ ላይ ለፈጸመው ክሕደት ከእርሱ ጋር እፋረዳለሁ።


እኔም ድሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች