Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 2:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ፍቅርን ለመሻት መንገድሽን እንዴት በጥንቃቄ ታስተካክያለሽ! ስለዚህም ለክፉዎች ሴቶች እንኳ መንገድሽን አስተምረሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ፍቅርን ለመፈለግ እንዴት ሥልጡን ነሽ? ልክስክስ ክፉ ሴቶች እንኳ ከመንገድሽ ብዙ ክፋት ይማራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 አንቺ ፍቅረኞችሽን ተከትለሽ ለመሮጥ ምንኛ ብልኅ ሆንሽ? እጅግ ብልሹ የሆኑት ሴቶች እንኳ በአካሄድሽ ይመራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ፍቅ​ርን ለመ​ሻት እን​ግ​ዲህ በመ​ን​ገ​ድሽ የም​ት​ፈ​ል​ጊው መል​ካም ምን​ድን ነው? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ መን​ገ​ድ​ሽን ታረ​ክሺ ዘንድ ዳግ​መኛ በደ​ልሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ፍቅርን ለመሻት መንገድሽን እንዴት ታቀኛለሽ! ስለዚህ ለክፉዎች ሴቶች እንኳ መንገድሽን አስተምረሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 2:33
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንቺ በእነርሱ መንገድ መሄድሽና ርኩሰታቸውንም መከተልሽ ብቻ ሳይሆን፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመንገድሽ ሁሉ ከእነርሱ የበለጠ ምግባረ ብልሹ ነበርሽ።


እነሆ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቻለሁ፥ ድርሻሽንም ቀንሻለሁ፥ ከክፉ መንገድሽ የተነሣ ለሚያፍሩ፥ ለጠላቶችሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ።


መንገድሽን ለመለወጥ ለምን በጣም ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ እንዲሁ ያሳፍርሻል።


አንቺስ፦ ‘ራሴን አላረከስኩም በዓሊምንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ምን እንዳደረግሽም እወቂ፤ በመንገዶችዋ ላይ ወድያና ወዲህ የምትቅበዘበዥ ወጣት ግመል ሆነሻል፤


ምናሴም ጌታ ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ እንዲሠሩ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ።


ደስታዋንም ሁሉ፥ በዓላቶችዋንም፥ መባቻዎችዋንም፥ ሰንበቶችዋንም፥ የተቀደሱትንም ጉባኤዎችዋን ሁሉ አስቀራለሁ።


በውኑ ኰረዳ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጣጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን በቍጥር ለማይቆጠሩ ቀናቶች ረስተውኛል።


እንዲሁም ሲምሱ አልያዝሻቸውም ነገር ግን በልብሶችሽ ላይ የንጹሐን ድሆች ደም ተገኝቶአል፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ብትፈጽሚም እንኳ


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች