ኤርምያስ 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 በውኑ የሊባኖስ በረዶ የድጋያማውን ምድር ይተዋልን? ወይስ ከሩቅ የምትመጣው ቀዝቃዛይቱ ፈሳሽ ውኃ ትደርቃለችን? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 የሊባኖስ ተራራ ድንጋያማ ተረተር፣ በረዶ ተለይቶት ያውቃልን? ከጋራው የሚወርደውስ ቀዝቃዛ ውሃ፤ መፍሰሱን ያቋርጣልን? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 የሊባኖስ ጭንጫማ ተራራዎች በበረዶ ያልተሸፈኑበት ጊዜ አለን? ከየተራራው ላይ የሚወርዱትስ ቀዝቃዛ ምንጮች ደርቀው ያውቃሉን? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ምንጭ ከዓለት ይጠፋልን? በረዶስ ከሊባኖስ ይጠፋልን? ወራጅ ውኃስ በኀይለኛ ነፋስ ይመለሳልን? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በውኑ የሊባኖስ በረዶ የምድረ በዳውን ድንጋይ ይተዋልን? ወይስ ከሩቅ የምትመጣው ቀዝቃዛይቱ ፈሳሽ ውኃ ትደርቃለችን? ምዕራፉን ተመልከት |