ኤርምያስ 14:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የሜዳ አህዮችም በተራቈቱ ኮረብቶች ላይ ቆመዋል፥ እንደ ቀበሮም ወደ ነፋስ አለከለኩ፤ ልምላሜም የለምና ዐይኖቻቸው ጠወለጉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 የሜዳ አህዮች ባድማ ኰረብቶች ላይ ቆሙ፤ እንደ ቀበሮም አየር ፍለጋ አለከለኩ፤ ግጦሽ ባለመገኘቱ፣ ዐይኖቻቸው ፈዘዙ።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የሜዳ አህዮች ከውሃ ጥም የተነሣ፥ በየኰረብታው ጫፍ ላይ ቆመው እንደ ቀበሮ ያለከልካሉ፤ ምግብ ስለማያገኙም የማየት ኀይላቸው ይቀንሳል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የሜዳ አህዮችም በወና ኮረብታ ላይ ቆመዋል፤ እንደ ሰገኖም ወደ ነፋስ አለከለኩ፤ ሣርም የለምና ዐይኖቻቸው ጠወለጉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 የሜዳ አህዮችም በወና ኮረብታ ላይ ቆመዋል፥ እንደ ቀበሮም ወደ ነፋስ አለከለኩ፥ ልምላሜም የለምና ዓይኖቻቸው ጠወለጉ። ምዕራፉን ተመልከት |