Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 14:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለምን መታኸን? ፈውስስ ስለምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ተጸየፈቻትን? ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ፣ ለምን ክፉኛ መታኸን? ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም በጎ ነገር አላገኘንም፤ የፈውስን ጊዜ ተጠባበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እግዚአብሔር ሆይ! ይሁዳን ፈጽመህ ልትጥላት ነውን? የጽዮንንስ ሕዝብ እንደ ጠላህ መቅረትህ ነውን? ለመፈወስ እስከማንችል ድረስ፥ ይህን ያኽል እንድንጐዳ ማድረግህስ ስለምንድን ነው? ሰላም እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፥ ነገር ግን ምንም መልካም ነገር አልገጠመንም፤ ፈውስ እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ሽብር እየበዛ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በውኑ ይሁ​ዳን ፈጽ​መህ ጥለ​ኸ​ዋ​ልን? ነፍ​ስ​ህስ ጽዮ​ንን ጠል​ታ​ታ​ለ​ችን? ስለ ምን መታ​ኸን? ፈው​ስስ ስለ ምን የለ​ንም? ስለ ምን ተስፋ አደ​ረ​ግን? ነገር ግን መል​ካም ነገር አል​ተ​ገ​ኘም፤ የፈ​ው​ስን ጊዜ ተስፋ አደ​ረ​ግን፤ ነገር ግን ድን​ጋጤ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፥ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 14:19
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ፈጽመህ ጥለኸናል፥ እጅግ ተቈጥተኸናል።


ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ መፈወስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።


እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።


ጌታ ጥሎአቸዋልና ‘የተጣለ ብር’ ብለው ይጠሩአቸዋል።”


ሙግትህን የሚፈርድልህ የለም፥ ለቁስልህም መድኃኒት የለውም፥ ለአንተም ፈውስ የለህም።


ለምን ሕመሜ የማያቋርጥ ሆነ? ቁስሌስ የማይፈወስ ለምን ሆነ? ለምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆንብኛለህን?


ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን በእኔ ላይ አንሥታለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ።


እግዚአብሔርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ፥ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ፥


ነገር ግን በጎነትን ስጠባበቅ ክፉ ነገር መጣብኝ፥ ብርሃንን ተስፋ ሳደርግ ጨለማ መጣ።


ፌ። ዓይናችን ወደ ከንቱ ረዳታችን ገና ሲመለከት ጠፍቶአል፥ በመቆየታችን ማዳን የማይቻለውን ሕዝብ ጠብቀናል።


ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው?


ጌታም እንደዚህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም እንኳ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ።


በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለምን አልሆነም?


ጌታ የቁጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጉርሽን ቁረጪ፥ ጣዪውም፥ በተራቈቱ ኮረብቶችም ላይ ሙሾን አውጪ፥” ትላቸዋለህ።


ለዘለዓለም እንደ ጨረቃ ይጸናል፥ ምስክርነቱ በደመና የታመነ ነው።


እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


“ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።


በማሮት የምትቀመጠው መልካም ነገርን ትጠባበቃለችና፤ ነገር ግን ክፉ ነገር ከጌታ እስከ ኢየሩሳሌም በር ድረስ ወርዶአል።


ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስብራትህ የማይፈወስ ቁስልህም የማይሽር ነው።


ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፥ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ ዘንድ አልተተዉም።


ታው። እንደ በዓል ቀን የሚያስፈሩኝን ከዙሪያዬ ጠራህ፥ በእግዚአብሔር ቁጣ ቀንም ያመለጠ ወይም የቀረ አልተገኘም፥ ያቀማጠልኋቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ በላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች