Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 11:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ከመከራቸው የተነሣ ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አልሰማቸውምና ስለ እነርሱም ጩኸትና ልመና አታድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “በተጨነቁ ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ልመና አታቅርብ፤ አትማጠን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ኤርምያስ ሆይ፥ እነርሱ በሚጨነቁበት ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ ስለማልሰማቸው ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ስለ እነርሱም ልመናና ምልጃ አታቅርብ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አን​ተም ስለ​ዚህ ሕዝብ አት​ጸ​ልይ፤ በመ​ከ​ራ​ቸው ቀን ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምና ስለ እነ​ርሱ አት​ጸ​ልይ፤ በም​ል​ጃና በጸ​ሎት አት​ማ​ልድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፥ ከመከራቸው የተነሣ ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አልሰማቸውምና ስለ እነርሱም ጩኸትና ልመና አታድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 11:14
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እንግዲህም አልሰማህምና ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፤ አትማልድላቸው።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሊያመልጡት የማይችሉትን ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ፥ ወደ እኔም ይጮኻሉ፤ እኔም አልሰማቸውም።


ማንም ወንድሙ ለሞት የማያደርስ ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ እግዚአብሔርም ለሞት የማያደርስ ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ። ስለዚህ ይለምን አልልም።


ጌታም፦ “ለዚህ ሕዝብ ስለ መልካም አትጸልይላቸው።


አሁንም ቁጣዬ በእነርሱ ላይ እንዲነድና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ ከአንተም ታላቅ ሕዝብ አደርጋለሁ።”


በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር።


ጌታንም ለመሻት በጎቻቸውንና በሬዎቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተመልሶአልና አያገኙትም።


ጌታም እንደዚህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም እንኳ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ።


እኔ ስጠራቸው እነርሱ አልሰሙኝም፥ እንዲሁ እነርሱ በሚጠሩኝ ጊዜ እኔ አልሰማቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ይህንም ደግሞ አድርጋችኋል፤ እግዚአብሔር ቁርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥ ከእጃችሁም በደስታ እንዳይቀበለው መሠዊያውን በእንባና በልቅሶ በኅዘንም ትከድናላችሁ።


በጾሙ ጊዜ ልመናቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም፤ ይልቁንም በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ” አለኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች