ኤርምያስ 10:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፤ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ድንኳኔ ፈርሷል፤ ገመዶቹም ሁሉ ተበጣጥሰዋል፤ ልጆቼ ጥለውኝ ሄደዋል፤ ከእንግዲህም አይመለሱም፤ ድንኳኔን ለመትከል፣ መጋረጃዬንም ለመዘርጋት ማንም የቀረ የለም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ድንኳኖቻችን ፈራረሱ፤ መወጠሪያ ገመዶችም ተቈራረጡ፤ ልጆቻችን በሙሉ ተሰደው ስለ ሄዱ፥ ድንኳኖቻችንን መልሶ የሚተክልልንና መጋረጃዎቻችንን የሚሰቅልልን አንድ እንኳ አልቀረም።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ድንኳኔም ተበዘበዘ፤ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆችና በጎችም የሉም ከእንግዲህ ወዲህ ለድንኳኔም ቦታ የለም ለመንጎችም መሰማሪያ የለም፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፥ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፥ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም። ምዕራፉን ተመልከት |