Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 10:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለምን በጥበቡ የመሠረተ፥ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እርሱ ግን ምድርን በኀይሉ ፈጠረ፤ ዓለምን በጥበቡ መሠረተ፤ ሰማያትንም በማስተዋሉ ዘረጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን ሠራ፤ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ ያጸና፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 10:12
38 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።


የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ከመኖሩ በፊት፥ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ከመብቀሉ በፊት፥ ጌታ እግዚአብሔር በምድር ላይ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም።


የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ ጌታ ግን ሰማያትን ሠራ።


ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም ያለአንዳች ድጋፍ ያንጠለጥላል።


እንደ ቀለጠ መስተዋት ብርቱ የሆኑትን ሰማያት ከእርሱ ጋር ልትዘረጋ ትችላለህን?


ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል።


ብርሃንን እንደ ልብስ ለበስህ፥ ሰማይንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፥


አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፥ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች።


እውነትህ ለልጅ ልጅ ናት፥ ምድርን መሠረትሃት እርሷም ትኖራለች።


እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም ላይ አጽንቶአታልና።


በጌታ ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ በአፉም እስትንፋስ ሠራዊታቸው ተፈጠረ፥


በጉልበትህ ተራሮችን አጸናሃቸው፥ በኃይልም ታጥቀሃል።


መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ፥ ለዘለዓለምም በምድር ውስጥ መሠረታት።


ጌታ ነገሠ፥ ግርማን ተጐናጸፈ፥ ጌታ ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፥ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት።


ጌታ በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና።


ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?


“አቤቱ የሠራዊት ጌታ፥ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አንተ ብቻህን የምድር መንግሥታት ሁሉ አምላክ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን ፈጥረሃል።


እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርሷም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥


ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፥ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፥ በእርሷ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፥ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ ጌታ እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?


እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርሷ ላይ ፈጥሬአለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።


ሰማያትን የፈጠረ ጌታ፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፥ እንዲህ ይላል፦ እኔ ጌታ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።


እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፤ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤ እጠብቅሃለሁ፥ ምድርንም እንድታቀና፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች እንድታወርስ፥


ድምፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፥ ከምድርም ዳርቻ ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናቡም መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።


የያዕቆብ ድርሻ እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙ የሠራዊት ጌታ ነው።


በውኑ በአሕዛብ ከንቱ ጣዖታት መካከል ዝናብን ሊያዘንብ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ካፊያን መስጠት ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ! አንተ አይደለህምን? አንተ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።


ምድሪቱን በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ለዓይኔም መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ።


‘አቤቱ ጌታ ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ በእውነት አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ለአንተም ከቶ የሚሳንህ ምንም ነገር የለም።


ስለ እስራኤል የተነገረ የጌታ ቃል ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ ጌታ እንዲህ ይላል፦


ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም ሁሉ አንድም ነገር ያለ እርሱ የሆነ የለም።


የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች