Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 1:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በብንያም አገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት የሆነ የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ ቃላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የኬልቅያስ ልጅ፣ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ አባቱ በብንያም አገር በዓናቶት ከሚገኙት ካህናት አንዱ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በብንያም ነገድ ርስት ውስጥ በምትገኝ ዐናቶት በምትባል መንደር ከሚኖሩ ካህናት አንዱ የሆነው የሕልቅያ ልጅ ኤርምያስ የተናገረው ቃል የሚከተለው ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በብ​ን​ያም ሀገር በዓ​ና​ቶት ከነ​በሩ ካህ​ናት ወገን ወደ ሆነ ወደ ኬል​ቅ​ያስ ልጅ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በብንያም አገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት የሆነ የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ ቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 1:1
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጌታ ቃል፥ በከለዳውያን አገር በኮቦር ወንዝ፥ ወደ ቡዚ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። በዚያም የጌታ እጅ በእርሱ ላይ ሆነች፥


ስለዚህም፦ “በእጃችን እንዳትሞት በጌታ ስም ትንቢት አትናገር” ብለው ነፍስህን ስለሚሹ ስለ ዓናቶት ሰዎች


በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።


እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።


የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ብሎ ላከ፦ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል አሢሮብሃል፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም።


የአሞጽ ቃላት፥ በቴቁሔ ከሚገኙ ከበግ አርቢዎች መካከል የነበረ፥ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየው ይህ ነው።


በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፤ በኢዮአታም፤ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን፤ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ።


የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፤


ያንጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ እንዲህ ሲል የተነገረው ተፈጸመ፤


እነርሱም “አንዳንዶቹ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎች ኤልያስ፥ ሌሎች ደግሞ ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ” አሉት።


በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተነገረው ተፈጸመ “ከእስራኤል ልጆች አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ወሰዱ፤


ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም” አለው።


ኤርምያስም ለኢዮስያስ የልቅሶ ግጥም ገጠመለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ በልቅሶ ግጥማቸው ስለ ኢዮስያስ ይናገሩ ነበር፤ ይህም በእስራኤል ዘንድ ወግ ሆኖ በልቅሶ ግጥም ተጽፎአል።


በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ፤ ከጌታም አንደበት የመጣውን ቃል በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊት ራሱን አላወረደም።


በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት፥ በኤርምያስ አፍ የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፥ ይህም በመንግሥቱ ሁሉ በአዋጅና በጽሑፍ እንዲያስነግር ነው፤


የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፤ ጩኺ! ላይሻ ሆይ፤ አድምጪ! ምስኪን ዓናቶት ሆይ፤ መልሺላት!


አሁንስ ትንቢት የሚነግራችሁን የዓናቶቱን ሰው ኤርምያስን ለምን አልገሠጽከውም?


የዓናቶት ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት።


ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።


ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል የርስቱን ድርሻ ከዚያ ለመቀበል ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች