ኢሳይያስ 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ጡቦቹ ወድቀዋል፤ እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤ የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤ እኛ ግን በዝግባ እንተካለን። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ሕዝቡ በሙሉ፣ ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች ይህን ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 የእስራኤል ሕዝብና በሰማርያ ከተማም የሚኖሩ ሁሉ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር መሆኑን ያውቃሉ፤ ሆኖም፥ ትዕቢተኞችና እልኸኞች ሆነው እንዲህ ይላሉ፦ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የኤፍሬም ሕዝብ ሁሉና በሰማርያ የሚኖሩ ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ ኵራትም እንዲህ ይላሉ፦ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9-10 በትዕቢትና በልብ ኵራት፦ ጡቡ ወድቆአል፥ ነገር ግን በተወቀረ ድንጋይ እንሰራለን፥ የሾላ ዛፎች ተቈርጠዋል፥ ነገር ግን ዝግባን እንተካባቸዋለን የሚሉ በኤፍሬምና በሰማርያ የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ ያውቃሉ። ምዕራፉን ተመልከት |