Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፤ ድንቅ መካር፤ ኀያል አምላክ፤ የዘለዓለም አባት፤ የሰላም ልዑል ይባላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የወራሪ ጦረኞች ጫማና በደም የተለወሰ ልብሳቸው ሁሉ በእሳት ይጋያል። እንደ ማገዶ ሆኖ ይቃጠላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በደም የተ​ለ​ወሰ ልብስ በእ​ሳት ከሚ​ቃ​ጠል በቀር ለም​ንም አይ​ጠ​ቅ​ምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የሚረግጡ የሠልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 9:5
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤


“እኔ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን ለመሸከም የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤


የጅራፍ ድምፅ፥ የመንኰራኵር ድምፅ፥ የፈረስ ኮቴ፥ የሠረገላ መንጓጓት ተሰምቶአል፤


በተራራ ላይ እንዳሉ ሰረገሎች ድምፅ፥ ገለባውንም እንደሚበላ እንደ እሳት ነበልባል ድምፅ፥ ለሰልፍም እንደ ተዘጋጀ እንደ ብርቱ ሕዝብ ያኰበኩባሉ።


ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የጌታም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።


የጌታን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ።


ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤


ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ያጥባል፤ ኢየሩሳሌምንም ከተነከረችበት ደም በፍርድና በሚያቃጥል መንፈስ ያነጻታል።


ሳኦል ለካህኑ በመናገር ላይ ሳለ፥ በፍልስጥኤማውያን ሰፈር ሁካታው እየጨመረ ሄደ። ስለዚህ ሳኦል ካህኑን፥ “እጅህን መልስ” አለው።


ካህኑም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ማዕድ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ስቡ ሁሉ ለጌታ ነው።


ካህኑም ለጌታ በእሳት ላይ የሚቀርብ ማዕድ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።


እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።


ከኃይለኞች ፈረሶቹ የኮቴያቸው ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መንጐድ፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ወደ ልጆቻቸው ዘወር ብለው አይመለከቱም።


የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።


በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፤ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ! በመንግሥታትም መካከል፤ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል።


በጽድቅ፥ ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ።


እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።


የጦረኞች ጫማ ሁሉ፤ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፤ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም።


ለመንግሥቱ ስፋት፤ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፤ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዘለዓለም አባት ቅናት ይህን ያደርጋል።


ስለዚህ ያዕቆብ፦ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሆኖም ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ጵኒኤል” ብሎ ጠራው።


በፊቱ ተጠንቀቅ፥ ቃሉንም አድምጥ፤ ስሜ በእርሱ ስለ ሆነ ብትተላለፉ ይቅር አይልምና አታስመርረው።


የጌታም መልአክ፥ “ስሜ ድንቅ ስለ ሆነ፥ ለምን ትጠይቀኛለህ?” አለው።


“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።


አንቺ ግን ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትንሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


እርሱ የጌታን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይጐናጸፋል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ሰላማዊ መግባባት ይኖራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች