ኢሳይያስ 9:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 በሠራዊት ጌታ ቁጣ ምድር ትጋያለች፤ ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመር ማገዶ ይሆናል፤ ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾኽንና ኵርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነድዳል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዐምድ ይቆማል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 የሕዝቡ ክፋት ኲርንችቱንና እሾኹን እንደሚያቃጥል እሳት ነው፤ እንደ በረሓ እሳት ደኑን በሚያቃጥልበት ጊዜ ጢሱ ተትጐልጒሎ ሲወጣ ቀጥ ብሎ የቆመ ዐምድ ይመስላል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ኀጢአት እንደ እሳት ይነድዳል፤ እሳት እንደ በላችው ደረቅ ሣር ይቃጠላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃጠላል፤ በተራራዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃጠላል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፥ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፥ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፥ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል። ምዕራፉን ተመልከት |