Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 8:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ልትቀድሱ የሚገባው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ብቻ ነው፤ ልትፈሩት የሚገባው እርሱን ነው፤ ልትንቀጠቀጡለት የሚገባውም እርሱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የምትቀድሱት እርሱ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የምትፈሩት እርሱ ይሁን፤ የምትንቀጠቀጡለትም እርሱ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እኔ የሠራዊት አምላክ ቅዱስ እንደ ሆንኩ አስቡ፤ መፍራት የሚገባችሁም እኔን ብቻ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ነገር ግን የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀድ​ሱት፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ች​ሁና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ች​ሁም እርሱ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ነገር ግን የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፥ የሚያስፈራችሁና የሚያስደንግጣችሁም እርሱ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 8:13
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎን እላችኋለሁ እርሱን ፍሩ።


ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን እርሱን ፍሩ።


የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ፈረሶች አንቀላፉ።


ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ነበረ፤ እንዲያከብረኝ እነርሱን ሰጠሁት፤ እርሱም አከበረኝ፥ ከስሜም በማክበር ፈራኝ።


ነገር ግን የእጄን ሥራ ልጆቹን በመካከሉ ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።


የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ፥ የአባታቸውም አምላክ፥ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ ፍርሃት ማለ።


ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ በእምነት በረታ እንጂ፤ እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ አልተጠራጠረም።


እናንተ በጺን ምድረ በዳ ማኅበሩ በተገዳደረኝ ጊዜ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና።” ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው።


ሙሴም አሮንን፦ “ጌታ፦ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ዝም አለ።


ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ ሊፈትናችሁ፥ ኃጢአትንም እንዳትሠሩ እርሱን መፍራት በልባችሁ እንዲሆን እግዚአብሔር መጥቷልና።”


ምንጊዜም ጌታ እግዚአብሔርን ማክበር ትማር ዘንድ፥ የወይን ጠጅና የዘይትህን አሥራት፥ የቀንድ ከብትህን፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት ስሙ እንዲጠራበት በሚመርጠው ስፍራ፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበላለህ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍትሕ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱሱም አምላክ ቅድስናውን በጽድቅ ይገልጻል።


ምድርን እንደሚሸፍን ደመና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። ጎግ ሆይ፥ በአንተ በኩል ቅድስናዬን በፊታቸው በምገልጥበት ጊዜ፥ አሕዛብ እንዲያውቁኝ፥ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።


እኔም በእስራኤል ልጆች መካከል እንድቀደስ የተቀደሰውን ስሜን አታርክሱ፤ የምቀድሳችሁ እኔ ጌታ ነኝ።


ጥንድ በሬዎች ወስዶ ቆራረጠ፤ ሥጋቸውንም በመልእክተኞች እጅ ልኮ፥ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ሰው በሬው እንደዚህ ይቆራረጣል!” ሲል በመላው እስራኤል አስነገረ። ታላቅ ፍርሀት ከጌታ ዘንድ በሕዝቡ ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች