ኢሳይያስ 7:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ኩርርንችትና እሾኹን በመፍራት ከዚህ በፊት በመቈፈሪያ ተቈፍረው ወደነበሩት ወደ እነዚያ ኰረብታዎች ሁሉ ከእንግዲህ አትሄድም፤ ነገር ግን የከብቶች መሰማሪያና የበጎች መፈንጫ ቦታ ይሆናሉ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ኵርንችትና እሾኹን በመፍራት ከዚህ በፊት በመቈፈሪያ ተቈፍረው ወደ ነበሩት ወደ እነዚያ ኰረብቶች ሁሉ ከእንግዲህ አትሄድም፤ ነገር ግን የከብቶች መሰማሪያና የበጎች መፈንጫ ቦታ ይሆናሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ቀድሞ በዶማ ተቈፍረው እህል ይበቅልባቸው የነበሩ ኰረብቶች ሁሉ ኲርንችትንና እሾኽን በመፍራት ማንም ወደዚያ አይሄድም፤ ነገር ግን የከብትና የበግ መንጋ መሰማሪያ ብቻ ይሆናሉ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 በሚታረሰውም ተራራ ሁሉ ላይ ፍርሀት ይመጣል፤ የበጎች መሰማርያ ይሆናል፤ በሬዎችም ይረግጡታል፤ እሾህና ኵርንችትም ያጠፋዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 በመቈፈርያም ወደ ተቈፈሩ ኮረብቶች ሁሉ ከኵርንችትና እሾህ ፍርሃት የተንሣ ወደዚያ አትሄድም፥ ነገር ግን የበሬ ማሰማርያና የበግ መራገጫ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከት |