Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 64:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፥ አንተ ወረድህ፥ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እኛ ያልጠበቅነውን አስፈሪ ነገር ባደረግህ ጊዜ፣ አንተ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከዚህ በፊትም መጥተህ እኛ ያልጠበቅናቸውን እጅግ አስፈሪ የሆኑ ነገሮችን በፈጸምክበት ጊዜ ተራራዎች አንተን አይተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የክ​ብ​ር​ህ​ንም ሥራ ባደ​ረ​ግህ ጊዜ፥ ተራ​ሮች በፊ​ትህ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፥ ወረድህ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 64:3
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፥ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክቶቻቸውን ከፊቱ አሳዶ ታላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?


እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው፥ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።


ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ፥ ከሰው ልጆች ይልቅ በግብሩ ግሩም ነው።


አቤቱ፥ በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ፥ በምድረ በዳም ባለፍህ ጊዜ፥ ምድር ተናወጠች፥


ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ፥ በዙሪያው ያሉ ሁሉ ለሚያስፈራው እጅ መንሻን ያስገቡ።


እርሱም እንዲህ አለው፦ “እነሆ እኔ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉና በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገ ተአምራት ፊት አደርጋለሁ፤ እኔ በአንተ የምሠራው ነገር የሚያስፈራ ነውና በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝብ ሁሉ የጌታን ሥራ ያያል።


የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።


ምነው ሰማያትን ቀደህ ብትወርድ! ምነው ተራሮችም ቢናወጡ!


እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፓራን ተራራ መጣ። (ሴላ) ውበቱ ሰማያትን ሸፍኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።


ቆመ፥ ምድርንም አንቀጠቀጣት፥ ተመለከተ፥ ሕዝቦችንም አስደነገጠ፥ የዘለዓለም ተራሮች ተናጉ፥ የጥንት ኮረብቶች አጎነበሱ፥ የጥንት መንገዶች የእርሱ ናቸው።


ዐይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቅና የሚያስፈሩ ነገሮችን ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱ አምላክህ ነው።


ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች